ደበሎ የአብነት ትምህርት ቤት በኢንተርኔት

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ደበሎ የአብነት ትምህርት ቤት በኢንተርኔት

በነጻ የቤተክርስቲያናችንን የአብነት ትምህርት (ቆሎ ትምህርት) በንባብ፣ በዜማ፣ የሃይማኖት መጽሐፍትን በፒዲኤፍ እና በድምጽ የሚያገኙበት ድረ ገጽ ነው። በውስጡም ብዛት ያላቸው የድምጽ እና የጽሑፍ ትምህርቶችን የያዘ ሲሆን፣ ለዲያቆናትም ግብረ ዲቁና የሚማሩበት ክፍልም አለው። ድረገጻችን እስከ አሁን የሚከተሉትን በድምጽ እና በጽሁፍ የቀረቡ ትምህርቶች ሲኖሩት ለወደፊትም በበለጠ ለመስራት እንችል ዘንድ ሁላችሁም በጸሎት አስቡን። ማንኛውም አስተያየት ካለዎት ይህንን በመጫን ያግኙን

የአብነት ትምህርት ቤት በኢንተርኔት

አብነትትምህርት ቤት ማለት ከአባት የተገኘ ከአበው የተወረሰ ከጥንትየነበረ የማንነት መገለጫ በራስ ቋንቋ በራስ ፊደል በራስ ሥራተ ትምህርትየሚሰጥ ከትውልድ ወደ ትውልድ የተላለፈ ትምህርት የሚሰጥበት ትምህርት ቤት ማለት ነው ። የአንድን ሕዝብ የአንድን ሀገር ጥበብ እና ዕውቀት ለዚያሕዝብ እና ለዚያች ሀገር ዜጎች የሚያስተምሩበት ትምህርት ቤት ማለት ነው ። ሥርዐተ ትምህርቱ አገር በቀል በሆኑ ብሔራውያንሊቃውንት ተዘጋጅቷል ። ከጊዜ ወደ ጊዜም ዳብሯል ። የአብነት ትምህርት ቤት በልማድ "የቆሎትምህርት ቤት " በመባል በሕዝባችን ዘንድ ይታወቃል ። አንዳንድ ሰዎች ደግሞ "የቄስ ትምህርት ቤት " እንዲሁም አንዳንዶች " የቤተ ክህነት ትምህርት ቤት " ይሉታል ።የመጀመሪያው ልማዳዊ ስያሜ የተማሪዎቹን አመጋገብና የችግር ኑሮ የሚገልጥ እንጅ የትምህርት ቤቱን ማንነት እና ዓላማ የማያሳይ በመሆኑ ተቀባይነት ያለው ስያሜ አይደለም ። ተጨማሪ ያንብቡ